የአክሱም የከተማ ውበትና ፅዳት

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከአክሱም ከተማ ማዘጋጃ ቤትና Sustainable Sweden Association ከተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመሆን የከተማዋን ውበትና ፅዳት ለመጠበቅ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ድህረ ምረቃ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉጌታ በሪሁ የአክሱምን ፈጣን የከተማ እድገትና የህዝብ ብዛት የሚመጥን ዘመናዊ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት በመዘረጋት የከተማዋን የቱሪዝም ተጠቃሚነት ለማሳደግና ለኑሮ ተመራጭ ለማድረግ የሚያስችሉ ጥናቶች እየተካሄዱ ነው፡፡ ዶ/ር ሙሉጌታ Sustainable Sweden Association ለማዘጋጃ ቤቱ ለባለሙያዎችና ለከተማው ነዋሪዎች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው በተለይ በኢኮቱሪዝም፣ በከተማ ውበትና ፅዳት እንዲሁም በአቅም ግንባታ ዙሪያ ተጨባጭ ጥናቶች አካሂዶ ወደ ተግባር ለመግባት በዝግጅት ላይ ነው፡፡

[metaslider id=1326]

Written by