Todays Post

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በዚህ ኣመት ለመጀመርያ ግዜ የተቀበላቸው 18 የድህረ ምረቃ ሪዚደንሲ ፕሮግራም ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲው ኘሬዚደንት ኘ/ር ገብረየሱስ ብርሀነ ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ኣመራሮች በተገኙበት የእንዃን ደህና መጣቹ ዝግጁት ኣድርገዋል።

በዝግጁቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ኮምኘሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ሃላፋ ዶ/ር ገ/ሂወት ተ/ሃይማኖት ለሬዚደንት ሃኪሞች እንዃን ደህና መጣቹ ካሉ በሃላ ኘሮግራሙ መጀመሩን ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረላቸውና የስፔሻሊቲ ኘሮግራም እንዲከፈት ከፍተኛ ኣስተዋፅኦ ለዳረጉ ኣካላት ምስጋና ካቀረቡ በሃላ ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ኮምኘሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በትግራይ ክልል የሚገኙ ሰውሰት ዞኖች ማለትም ማእከላይ ፣ ሰሜን ምዕራብ እንዲሁም ምዕራብ ትግራይ ለሚገኙ ከ 3.5 ሚልዬን በላይ ማህበረሰብ የምያገለግል መሆኑ የተሻለ ክህሎት እና እውቀት ማግኘት እንደምያስችላቸዉ በመግለፅ ለሬዚደንቶቹ የተሳካ የትምህርት ቆይታ እዲኖራቸው ተመኝቷል።

በመቀጠል የዩኒቨርሲቲው ኘሬዚደንት ኘ/ር ገብረየሱስ ብርሃነ ሬዚደንት ሃኪሞችን እንዃን ደህና መጣቹ ካሉ በሃላ ኘሮግራሙ መጀመሩ የህክምና ኣገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ከፍተኛ ኣስተዋፅኦ እንደሚኖረው ጠቁሟል። ኣያይዘውም ኘረዚደንቱ በትምህርት ቆይታቸው የተሳካ ግዜ እንዲኖራቸው ዩኒቨርሲቲው የሚችለውን ሁሉ ለማገዝ ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁሟል።

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ኣካዳሚክ እና ምርምር ምክትል ኘሬዚደንት ዶ/ር ሙሉጌታ በሪሁ ለትምህርታችሁ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር በሚኖራችሁ ቆይታ ከታካሚዎች እና ከሆስፒታሉ ሰራተኛች ጋር ተግባብታችሁና ተቀናጅታችሁ መስራትና መማር ፤ግብአቶችን በአግባቡ በመጠቀም እና መረጃን ማደራጀት ይጠበቅባችኋል በማለት አስገንዝበዋል።

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኣካዳሚክ እና ምርምር ዋና ዳሬክተር መምህር ተክለሃይማኖት ሕሉፍ በአራት የሪዝደንሲ ትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን የተቀበለው ዩኒቨርስቲው ቀጣይ በሚኖራቸው ቆይታ የመማር ማስተማር እና አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን አስመልክቶ ማብራሪያና ገለፃ አድርገዋል።

በመጨረሻ የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ና ኮምኘሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የድህረ ምረቃ ኣስተባባሪ ዶ/ር ገብረኣብ ነጋ ሃኪሞቹ በትምህርት ቆይታቸው የኣእምሮ ና ኣካለዊ ዝግጅት ከስነምግባር ባማጣመር ስኬታማ ግዚ እንዲኖራቹው ጠቁሟል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ኮምኘሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

ሚያዝያ 17 2016 ዓ/ም

Written by 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *