የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ለህግ ታራሚዎች የህግ ፣ የስብአዊ መብትና የስነ ልቦና ስልጠና ሰጠ ፡፡
ስልጠናዉ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በሽሬ እንዳስላሴ ማረሚያ ቤት ለሚገኙ ከ2600 በላይ ታራሚዎች የተሰጠ ሲሆን በሕይወት ክህሎት፣ በሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ፣ በህገ መንግስት ፅንስ ሃሳብ ፣ በህግ ታራሚዎች መብት እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ፡፡
የማረሚያ ቤቱ አዛዥ ኮማንደር ይርጋ በርሀ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለአከባቢዉ ህብረተሰብ እየሰጠ ያለዉ የማህበረሰብ አገልግሎት የሚመሰገን መሆኑን በመግለፅ አሁንም በማረሚያ ቤቱ በተደጋጋሚ ወንጀል በመፈፀም ታስረዉ የሚገኙትን ታራሚዎች ልዩ ድጋፍና ክትትል በማድረግ እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል ፡፡