በአክሱም ዩኒቨርስቲ የቃልኪዳን ቤተሰብ እና የቃልኪዳን ተማሪዎች የርክክብ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 21/2018 ዓ/ም

የሰላም ሚኒሰትር ከትምህርት ሚኒሰትር ጋር በመተባበር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቃልኪዳን ቤተሰብ፣ የቃልኪዳን ተማሪዎች ከአክሱም ከተማ አስተዳደር ተወካዮች በተገኙበት የርክክብ መርሃ ግብር ተካሄዷል ።

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአክሱም ዩኒቨርሲቲው ፕረዚዳንት ፕሮፈሰር ገብረየሱስ ብርሃነ የቃልኪዳን ቤተሰብ እና የቃልኪዳን ተማሪዎች ቀደም ሲል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተሞክሮ ውጤታማ በመሆኑ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም እንዲተገብሩ ከስምምነት መድረሱን ይታወሳል፤ እንዲሁም ወደ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት የሚመጡ ተማሪዎች በቆይታቸው ግዜ የብቸኝነት ስሜት እንዳይሰማቸው የሚያደርግ ከመሆኑ ባሻገር የውንድማማችነትን ትስስር የሚያጠናክር መሆኑን ገልጿል ።

በተጨማሪም በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልእክታቸውን ያስተላለፉት የአክሱም ከተማ የብዛህነት እና ግንኙነት ዞን ተወካይ አቶ ሰለሙን አለሙ በበኩላቸው የቃልኪዳን ቤተሰብ የርክክብ መርሃግብር እጅግ በጣም ጠቃሚ እና ወሳኝ መርሃግብር መሆኑን የገለፁት ሲሆን ተማሪዎች በቆይታቸውም ወቅት የባይተዋርነት ስሜት እንደማይሰማቸው ከማድረጉም በላይ በቀጣይም ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክር መርሃግብር መሆኑን አክለው ገልፀዋል።

የመርሃግብሩ አስተባባሪ ዶ/ር ታረቀኝ አብርሃ ሪፓርት ያቀረቡ ሲሆን ተማሪዎች የባህል፣እምነት፣ቋንቋ ልዩነት እንኳን ቢኖር ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዲከተሉና የብቸኝነት መንፈስ እንዳይ ሰማቸው ማድረግ አስፈላጊ ሲሆን በቆይታቸው ወቅትም መቻቻልን ፣አንድነት ፣ፍቅርን የተለያዩት ባህልና ቋንቋን ለምደው ይወጣሉ ሲሉ ገልፀዋል ።

በመጨረሻም ከሁሉም የሃይማኖቶች ተወካዮች፣ ከሴቶች እንዲሁም ከተማሪዎች የተሰማቸው ሰሜት በመግለፅ ፤ የአክሱም ከተማ የብዛህነት እና ግንኙነት ተወካይ ወ/ሮ ሙሉ ካሕሳይ ሀሳባቸውን በማጋራት የርክክብ መርሃግብሩ ተጠናቋል።

ልህቀት በጥረት!

ኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ

Written by 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *