ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ የሽኝትና የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ

አክሱም ዩኒቨርሲቲ፤ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም (ህ.አ.አ.ግ)

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ሳምንታት በስድስት ዙሮች በበይነ መረብ (Online) ሲሰጥ የቆየው የ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በላቀ ስኬት ተጠናቋል።

ይህንኑ አስመልክቶ ለሱፐርቫይዘሮች፣ ለፈታኝ መምህራን እና ለፌደራል ፖሊስ አባላት የሽኝት፣ የምስጋናና የእራት ፕሮግራም ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ገብረየሱስ ብርሃነ፣ ፈተናው ያለምንም እንከን ሙሉ በሙሉ በኮምፒዩተር (CBT) ተካሂዶ በስኬት መጠናቀቁ የዩኒቨርሲቲውን ጠንካራ የቴክኖሎጂ አቅም ያረጋገጠ መሆኑን ገልፀው ፤ ለሂደቱ መሳካት የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉት ለትምህርት ሚኒስቴር፣ ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ፣ ለፈታኞች፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለ ICT እና ቴክኒክ ባለሙያዎች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በሙሉ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

በተጨማሪም የሀገራዊ ፈተናዎች አስተባባሪ ዶክተር መሐመድ አሕመድ፣ የትምህርት ሚኒስቴር የማዕከል አስተባባሪ አቶ አለልኝ አሩቴ እና የፌደራል ፖሊስ ተወካይ ኢንስፔክተር ባስተላለፉት መልእክት፤ ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የሁሉም አካላት የተቀናጀ ሥራና የቅንጅት ውጤት መሆኑን ገልፀዋል።

በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ ለትምህርት ሚኒስቴር፣ ለፌደራል ፖሊስና ለተለያዩ አስተባባሪዎች የእውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

ልህቀት በጥረት!

አክሱም ዩኒቨርሲቲ

Written by 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *