አክሱም ዩኒቨርሲቲ | ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም.
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ልማት የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት በማንፀባረቅ በሁሉም ካምፓሶቹ የተሳካ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ።
በዋናው ግቢ አስቀድመው በተዘጋጁ የመትከያ ሥፍራዎች በተካሄደው በዚህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ገብረየሱስ ብርሃነ፣ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር አብርሃም ነጋሽ፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር መኮንን አረጋይ፣ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች በንቃት ተሳታፊ ሆነዋል።
የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቀነስ፣ የአካባቢን ውበትና የአየር ንብረት ማሻሻል፣ ለሥራ ምቹና ጤናማ አካባቢን መፍጠር እንዲሁም ለቀጣዩ ትውልድ የተጠበቀ ዘላቂ ሥነ-ምህዳርን ማቆየት እንደሆነ ተገልጿል። በወቅቱም አመራሮቹ ባስተላለፉት መልዕክት ችግኞችን ከመትከል ባለፈ ተገቢውን ክትትልና እንክብካቤ በማድረግ ማፅደቅ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።
“ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የነገውን ሕይወት ያለመልማል” በሚል እምነት ሙሉው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የተተከሉ ዕፅዋትን በመንከባከብና አካባቢን በመጠበቅ ረገድ የጋራ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
ልህቀት በጥረት!
አክሱም ዩኒቨርሲቲ
