20ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተከብሯል ።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ፣2018 ዓ/ም

20ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ ተከብሯል ።

በበዓሉ መክፈቻ የኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ የቃል ኪዳን ቤተሰብ አስተባባሪ ዶ/ር ታረቀኝ ኣብርሃ ተገኝተው ለበዓሉ ተሳታፊዎች የእንኳን በዳህና መጣችሁ እና የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ኣስተላልፏል።

የተማሪዎች ህብረት ፕረዚዳንት ተማሪ ፍቅረይ ጠዓመ በበኩሉ ይህ በዓል ከሌሎች ቦታዎች በተለየ በዩኒቨርሲቲ ሲከበር ”ልዩ ውበት” ይሰጣል፤ ምክንያቱም ዩኒቨርሲቲ የታላቅዋ ኢ/ያ ተምሳሌት “ትንሽዋ “ኢ/ያ ናት። ስለዚህም እንደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይህንን በዓል ስናከብር በመተሳሰብ ፣መከባበር ፣ፍቅርና ኣንድነትን ታሳቢ ኣድርገን አብሮ መኖርን የምንማርበት ልዩነታችን እንደውበታችን ቆጥረን ኣብረን የምናጌጥበት ምክንያት ጌጣችን መሆን ኣለበት የሚል መልእክት አስተላልፏል፤ በተጨማሪ “በመተሳሰብ ኣብረን የነገ ህይወታችን እንገንባ “ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ”ህብረ ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት በኢትዮጵያ ተግዳሮቶች” የመፍትሔ ሃሳቦች የሚል ፅሑፍ በመ/ር ሓጎስ ትኩእ ከስነምግባር እና ስነዜጋ ትምህርት ክፍል የመወያያ ፅሑፍ ቀርበዋል ።

በመጨረሻ ተማሪዎችን የሚያዝናኑ የብሄር ብሄረሰቦች ሙዚቃ በመጋበዝ ዝግጅቱን ተጠናቅቋል ።

ልህቀት በጥረት!

ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ

Written by