ኣኽሱም ዩኒቨርስቲ ታሕሳስ 6 እና 7 /2018 ዓ/ም የ Remedial (ሪሜድያል ) ተማሪዎች በደማቅ ሁኔታ ይቀበላል።

ዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር እንቅስቃሴውን እየቀጠለ እና የአቅም ማሻሻያ (Remedial ) ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቆ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርስቲው ከመላው አገሪቱ የመጡ ተማሪዎች ተቀብሎ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እያከናወነ ሆኖ፤ ተማሪዎቻችን በጥንታዊቷ፣ ታሪካዊቷ እና ውቢትዋ ኣኽሱም ከተማ እንዲሁም ኣኽሱም ዩኒቨርስቲ ቆይታቸው በሰላም ፣በፍቅር ፣በአንድነት እና መቻቻልን እየኖሩና እየተማሩ ይገኛሉ። ስለሆነም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች አክሱም ዩኒቨርስቲ የተመደባቹ ውድ ተማሪዎቻችን ከወዲሁ ወደ ሁለተኛ ቤታችሁ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በሰላም እንድትመጡ እንመኛለን ።

ልህቀት በጥረት!

ኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ

Written by