ዩኒቨርሲቲዎች የሰላም እሴቶችን በመገንባት ችግሮችን በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ መፍታት እንዳለባቸው ተጠቆመ

Selam.jpg

የፌደራል ኣርብቶ ኣደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የትግራይ ክልልግጭት መከላከልና የማእከላዊ ዞኑ ግጭት መከላከልና ከኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው በትግራይና በኣፋር ክልሎች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሰላም ፎረም የምክክር መድረክ ዛሬ ህዳር 9-2010 ዓ/ም በኣክሱም ከተማ ተጀመረ።

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ የኣካዳሚ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ የህዝቦች የጋራ ራእይ የሆነው ድህነትን የማስወገድ ስራ ስኬታማ የሚሆነው ኣስተማማኘ ሰላም ሲኖር በመሆኑ እያንዳንዳችን የሰላም እሴቶችን በመገንባት ሰላማችንን ማስጠበቅ ኣለብን ብለዋል።

የመድረኩ ዋና ኣላማ በሰላም እሴት ፅንሰ ሃሳብ ላይ ግንዛቤ በማሳደግና ልምዶች በመለዋወጥ ዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ የትምህርትና የልህቀት ማእከል እንዲሆኑ ማስቻል እንዲሁም የኢፌድሪ ሕገ-መንግስትና የፌደራል ስርኣቱ መርሆዎች በማጎልበት ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት በልዩነት ውስጥ ጠንካራ ኣንድነት መገንባት ሲሆን መድረኩን የከፈቱት የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፀጥታና የኣስተዳደር ጉዳዮች ሃላፊ ተወካይ ኣቶ ሃ/ሚካኤል ስዩም ሕገ-መንግስቱ የጣለብንን ኣንድ የጋራ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባት ኣላማ ተግባራዊ ለማድረግ ዲሞክራሲያዊ ብሄርተኝነትን በተላበሰ ሁኔታ በመከባበርና በመደጋገፍ የህዳሴያችንን ጉዞ ማሳካት ይግባል በማለት በኣንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የሚታዩ የመልካም ኣስተዳደርና የኣቅርቦት ችግሮች በሰለጠነ መንገድ በውይይት እንዲፈቱ የሰላም ፎረም ኣባላት የመፍትሔ ኣካል በመሆን እንዲሰሩ ኣሳስበዋል።