የፋይናንስና የአካውንቲንግ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስና የአካውንቲንግ መምህራን በአዲሱ የIFRS (International Financial Reporting Standards) ዙርያ ከኢትዮጵያ የአካውንቲንግና ኦዲቲንግ ቦርድ በመጡ ባለሞያዎች ስልጠና ተሰጣቸው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር-ቤት ባወጣው ደንብ ቁጥር 847/2014 መሰረት ነባሩ Generally Accepted Accounting Standards የሚባለው የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ስርዓት በአዲሱ የIFRS ስርዓት እንዲተካ የተወሰነ ሲሆን የኢትዮጵያ የአካውንቲንግና ኦዲቲንግ ቦርድ ስራውን እንዲያስፈፅም ሃላፊነት ሰጥቶታል፡፡

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን መምህር ሙሴ ተስፋይ አስር ቀናት በቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና ማብቂያ ላይ እንደተናገሩት ስልጠናው ያስፈለገበት ዋና ምክንያት አክሱም ዩኒቨርሲቲ በፋይናንስና አካውንቲንግ የትምህርት ዘርፎች የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በአዲሱ አሰራር መስራት ተገቢውን እውቀትና ክህሎች እንዲጨብጡ ለማድረግ ቅድሚያ የመምህራን ዝግጅት ለማከናወን ነው፡፡

በስልጠናው ላይ በአዲሱ የሂሳብ አያያዝ እውቀት ሊኖራቸው የሚገባ በአክሱም የሚገኙ የግል የሂሳብ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን እንደ መምህር ሙሴ ገለፃ ኮሌጁ ለአካባቢው ማህበረሰብ ከሚሰጠው ዘርፈ ብዙ ስልጠና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች አካል የሆነው በእንደዚህ አይነት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ ስልጠናዎች የአካባቢው ማህበረሰብ ከዩኒቨርሲቲው መምህራን ጋር ከስልጠናው ተጠቃሚ የማድረግ ጉዳይ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

Written by