የተቀናጀ ስራ የአረጋዉያንን ችግር ለመቅረፍ

አረጋዉያን ያለባቸዉን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር በመቅረፍ በዘላቂነት ለማቋቋም የተለያዩ በጎ ፍቃደኛ ድርጅቶችና ግለ ሰቦች የሚያደርጓቸዉ እንቅስቃሴዎች እንደሚደግፍ አክሱም ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ ፡፡

“በአከባቢያችን የሚገኙ አረጋዉያንን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረግ የምምክር መድረክና የመፍትሄ አቅጣጫ “ በሚል ሰሙኑን በተዘጋጀ መድረክ እንደተገለፀዉ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በጉዳዩ ዙርያ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመሆን በጋራ እንደሚሰራ አስታዉቋል ፡፡