ተማሪዎች በማህበረሰብ አገልግሎት ተሳተፉ

Student temari.jpg

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዉ ዙርያ ለሚገኙ አቅም ለሌላቸዉ አርሶ አደሮች ለአጨዳ የደረሱ ሰብሎቻችዉን  ነፃ የማህበረሰብ አገልግሎት በመስጠት ሰበሰቡ ፡፡ እነዚህ ከ200 በላይ የሆኑ ተማሪዎች በአርሶ አደሩ ማሳ ለአጨዳ የደረሰዉን ሰብል በመሰብሰብ ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ሊያደርስ ይችል የነበረዉ ከፍተኛ ጉዳት እንደተከላከሉላቸዉ ተጠቃሚዎች ተናግረዋል ፡፡በጎ ፍቃደኞቹን በማስባሰብ ለዚህ የተቀደሰ ተግባር ያስተባበራቸዉ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የሰላም ፎረም እና የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት ነዉ ፡፡