አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ቀናት የቆየ ስልጠና ለህዝብ ግኑኝነት ባለሙያዎች ሰጠ

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነትና ተግባብ ት/ት ክፍል በኩል ከትግራይ ኮምዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ቢሮ ጋር በመተባበር በታህሳስ 23 ቀን 2009 ዓ/ም ለሁለት ቀናት   የቆየ ስልጠና ለህዝብ ግኑኝነት ባለሙያዎች ሰጠ፡፡

አገራዊ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ቀዳሚ እንሁን በሚል መሪቃል ከተለያዩ የመንግስትና የግል መስርያ ቤቶች ለተዉጣጡ የህዝብ ግንኙነትና የሚድያ አመራር በልማታዊ ጋዜጠኝነትና የህዝብ ግንኙነት ሥራና የግጭት አፈታት ዙርያ ነው ስልጠናው የተሰጠው::

በስልጠናው የኢፌድሪ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ “መገናኛ ብዙሃን የህብረተሰቡ ፍላጎት መሰረት ያደረገ አሳታፊ የመረጃ ስርጭት ሊኖራቸዉ ይገባል” ብለዋል፡፡

በስልጠናዉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕረዚዳንት ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ዩኒቨርሲቲዉ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚድያና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች አቅም በመገንባት የህብረተሰቡ የመረጃ ፍላጎት ለማሟላት እየሰራን ነዉ ብለዋል::

የትግራይ ኮምዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ቢሮ ሃላፊ አቶ ገብረሚካኤል መለስ በበኩላቸዉ የትግራይ የመገናኛ ብዙሃንና የህዝብ ግንኙነት አሰራር ለማሻሻል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በትብብር እየተዘጋጀ መሆኑ ገልጸዋል::

Written by