የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ የፈሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ማእከል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ግንባታዉ ነሐሴ 2005 ዓ/ም የተጀመረዉ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ የፈሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ማእከል አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

ይህ የዩኒቨርሲቲዉ የቆሻሻ ማጣሪያ ከ81 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ በርሀ መስፍን ገልፀዋል። ከተለያዩ ክፍሎችና ከተማሪዎች መፀዳጃና መታጠቢያ ቤቶች የሚወገደዉ ከፍተኛ መጠን ያለዉ የፈሳሽ ቆሻሻ በዘመናዊ መንገድ በማስወገድ የግቢዉ ንፅህና በመጠበቅ ለዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ የተመቻቸ የስራ እና የጤና አከባቢ ከመፍጠሩም ባሻገር በማጣሪያዉ ሂደት የሚወጣዉ ዉሃ ለመስኖ አገልግሎት ይዉላል፡፡ ግንባታዉ የትምህርት ሚኒስቴርን ወክሎ ያሰራዉ የጀርመን የተራድኦ ድርጅት (ጂአይዜድ ) ሲሆን አማካሪዉ ደግሞ ኤም ኤች ኢንጀነሪንግ የተባለ ኩባንያ ነዉ፡፡

Written by