ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርትና የስልጠና ማእከላት ጥራት ያለዉ የሰዉ ሃይል እንዲያመርቁ ቀጣሪ ኢንዱስትሪዎች ጠየቁ ፡፡ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎትና ዩኒቨርሲቲ እንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት ትላንት ባሰናዳዉ በአክሱም ንኡስ ቀጠና የዩኒቨርሲቲ ኢንዳስትሪ ትስስር የምክክር መድረክ እንደተገለፀዉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያሰለጥንዋቸዉ ተማሪዎች በስራ ዓለም ካለዉ ተጨባጭ ነባራዊ ሃቅ ጋርበተግባር የሚዛመድ መሆን ይገባዋል ፡፡
[metaslider id=1008]
የንኡስ ቀጠናዊዉ ትስስር ጥቅምት 30/2008 ዓ/ም የተመሰረተ ሲሆን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች እና ሌሎች ኢንዱስትሪዎች የተለያዩ ስራዎች ሲያከናዉን ቆይቷል ፡፡
የትስስር ዋና አለማ በፎረሙ አባላት መካከል የጠነከረ ግንኙነት በመፍጠር በዉጤቱምርታማነትን በጥራትና በመጠን በመጨመር በሂደቱ የትምህርትና ስልጠና የምርምርና የማማከር ዓቅምን ማሳደግ ሲሆን በተሰናዳዉ የምክክር መድረክ እንደተገለፀዉ ትስስሩ እስካሁን በጅምር ያለ እና ወደ ሚፈለገዉ ደረጃ ያላደገ ነዉ፡፡ይሁንና የትስስሩ አባላት አሁን ያለዉን ሁኔታ ለመቀየር ትኩረት ሰጥተዉ እንዲሚሰሩ ገልፀዋል ፡፡