Happy New Year 2019 To the Aksum University Community/የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ለመላው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና ለውድ ህዝባችን፣

በመጀመሪያ እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም፣ በጤና እና በህያው ተስፋ አደረሳችሁ!

አዲሱ ዓመት የፅናት፣ የዕድገት እና የአዳዲስ ብሩህ ተስፋዎች በር የሚከፍት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ። ባለፈው ዓመት ያጋጠሙንን ፈተናዎች በጋራ በመሻገር፣ በትምህርት፣ በምርምር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች አጠናክረን የምንቀጥልበት ዓመት እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ።

በመሆኑም በነገው ዕለት የምንጀምረውን አዲስ መንፈስ እና ሀላፊነት በመያዝ፣ ዩኒቨርሲቲያችንን ወደ ላቀ የውጤታማነት እና የላቀ ተልዕኮ ደረጃ ለማድረስ ሁላችንም በጋራ፣ በትጋት እና በትብብር እንድንሰራ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የስኬት እና የምርታማነት ዓመት ይሁንልን!

መልካም አዲስ ዓመት!

ገብረየሱስ ብርሃነ (ፕሮፌሰር)

ፕሬዚዳንት፣ አክሱም ዩኒቨርሲቲ

Written by 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *