በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ለተመራቂ ተማሪዎች የሥራ ዕድል ፈጠራና የቅጥር ዝግጁነት ሥልጠና እየተሰጠ ነው

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሥራ ዕድል ፈጠራና የቅጥር ልማት ማዕከል ለዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ያዘጋጀው ልዩ የሥልጠና መርሃ ግብር ከዛሬ ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት ጀምሯል። የዚህ መርሃ ግብር ዋና ዓላማ ተማሪዎች የራሳቸውን የሥራ ዕቅድ፣ እሴቶችና ስብዕና በሚገባ እንዲረዱ ከማስቻሉም በላይ ጥንካሬና ድክመቶቻቸውን ለይተው በማወቅ ለሥራው ዓለም ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ መርዳት ነው። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 17/2018 ዓ.ም ድረስ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው ይህ ሥልጠና ተማሪዎች በአካባቢያዊ፣ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያዎች ውስጥ በብቃት ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ለግል የሥራ ዕድል ፈጠራም ሆነ ለቅጥር አስፈላጊ የሆኑ ክህሎቶችን እንዲጨብጡ አቅጣጫ የሚያሳይ ነው። በመጨረሻም የሥልጠናውን ሂደት ላጠናቀቁ ተማሪዎች ሁሉ የሥልጠና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት እንደሚሰጥ ታውቋል።

ልህቀት በጥረት!

አክሱም ዩኒቨርሲቲ

Written by