የአቅም ግንባታ ስልጠና

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከትግራይ ኢንፎርሜሽን እና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ለመጡ አንድ መቶ ሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮምፕዩተር ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኤጀንሲዉ ያወጣዉን የስልጠና ጨረታ ከሌሎች ተመሳሳይ የትምህርት ክፍል ካላቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተወዳድሮ በማሸነፍ ነዉ ስልጠናዉን እየሰጠ ያለዉ፡፡ በስልጠናዉ በትግራይ በሁሉም ወረዳዎች በሚገኙ የኤጀንሲዉ ፅ/ቤቶች የሚሰሩ የ (ICT) ባለሙያዎች በ Advanced CCNA, CISCO Hardware maintenance and troubleshooting and network device security ዙርያ የተግባር ስልጠና ነዉ እየተሰጠ ያለው፡፡

Written by