የሴቶች የአመራር አቅም ለማሳደግ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ

የአክሱም  ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የዩኒቨርሲቲዉ ሴቶች የአመራር አቅም ለማሳደግ ስልጠና እየሰጠ ነዉ ፡፡

   የሴቶችና ወጣቶች ጉዳዮች  ዳይሬክተሯ  ወ/ሮ አበባ አሰፋ ስልጠናዉ ትናንት  መጋቢት 19/2010 ዓ/ም ሽሬ ከተማ በሚገኘዉ የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳራሽ  ሲጀመር እንደተናገሩት የስልጠናዉ ዋና አላማ በዩኒቨርሲቱዉ ከከፍተኛ አመራር እስከ ቡድን መሪ ባሉ ሃላፊነቶች  የሚሰሩ ሴቶች የአመራር ( Leadership )  አቅም በማሳደግ እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲኖራቸዉ ማስቻል ነዉ ፡፡ ለአምስት ቀን በሚቆየዉ ስልጠና ከዋናዉ ግቢ ፣ ከሪፈራል ግቢ እና ሽሬ ግቢ የተዉጣጡ 70 መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሴቶች እየተሳተፉ ሲሆን ስልጠናዉን የሚሰጡት በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማኔጅመንት መምህር የሁኑት ዶ/ር ብርሃነ ሃ/ስላሴ ናቸዉ ፡፡