ለኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ/ም አዲስ ለተመደባቹ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ። በ2018 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ በ1ኛ አመት አዲስ ለተመደባቹ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል (Remedial) ትምህርታቹ ስትከታተሉ ቆይታችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግብያ ውጤት ያመጣቹ ተማሪዎች መግብያ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18 /2018 ዓ/ም መሆኑን አውቃቹ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እና ሪፖርት እንድታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።
ማሳሰብያ
- ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የ8ኛ ፣12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና የወሰዳቹበት ማስራጃ ዋናዉ እና ፎቶ ኮፒ፣ ከ9-12 ትራንስክሪፕት ዋናዉ እና ፎቶ ኮፒ ፣ 3*4 ስድስት ፎቶግራፍ፣ የመኝታ አልባሳት ፣ የስፖርት ትጥቆች እና ሌሎች ለመማር የሚያስፈልጉ ነገሮች ይዛቹ እንድትመጡ እናሳስባለን።
 - ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞ ወይም ዘግይቶ ለሚመጣ ማንኛውም ተማሪ የማናስተናግድ መሆናችን ከወዲሁ እንገልፃለን። የኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናው ሬጅስትራር ፅ/ቤት
 
