በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የእግር ኳስ ስፖርት ውድድር ፌስቲቫል እየተካሄደ ይገኛል

​አክሱም ዩኒቨርሲቲ፦ መጋቢት 08/2018 ዓ.ም ​በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ”ቱሪዝም ለሰላምና ለጋራ መግባባት” (Tourism for Peace and Societal Harmony) በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የተማሪዎች የእግር ኳስ ውድድር ፌስቲቫል ከመጋቢት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ​ይህ ስምንት ኮሌጆችን የሚያሳትፈው ስፖርታዊ መርሃ-ግብር፤ በተማሪዎች መካከል ያለውን ትስስር እና አንድነት ለማጠናከር እንዲሁም በአካልና በአእምሮ ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት ያለመ ነው። የቱሪዝም እና ሆቴል ማናጅሜንት ትምህርት ክፍል ሀላፊ መምህር ታሪኩ በቀለ እንደገለጹት፤ ስፖርት ለሰላም በሚል እሳቤ የሚካሄዱ መሰል ውድድሮች ተማሪዎች የአንድነት መንፈስ እንዲኖራቸውና የትውውቅ ጥንካሬ እንዲፈጥሩ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል። ​ውድድሩ እስከ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፣ በዕለቱም ለአሸናፊው ቡድን የዋንጫ ሽልማት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

Written by