በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የ11ኛ ሃገራዊ የምርምር ኮንፈረንስ ጥናታዊ ፅሑፍ ላቀረቡ መምህራን እና ተመራማሪዎች ሰርተፊኬት በመስጠት ተጠናቋል ።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ፣ታሕሳስ ፣17/2018 ዓ/ም

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ “በሳይንስና እና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ለማህበራዊ እድገት “(“Advance in Science,Technology and Innovation for Social Transformation “)በሚል መሪ ቃል ከታሕሳስ 16-17/2018 ዓ/ም ጀሚሮ በ11ኛው ሃገራዊ የምርምር ኮንፈረንስ ጥናታዊ ፅሑፍ ላቀረቡ ከዩኒቨርሲቲዎች እና በትግራይ ከሚገኙት የምርምር ኢንስቲትዩት የመጡ 14 መምህራን እና ተመራማሪዎች ሰርቲፊኬት በመስጠት ተጠናቋል ።

በዚህ የሰርቲፊኬት አሰጣጥ መድረክ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ገብረየሱስ ብርሃነ ተገኝተው ለምርምር አቅራቢዎች ፣ዘጋቢዎች ፣ለአዘጋጆች ኮሚቴ አባላት፣ የመድረኩ መሪዎች እና ተሳታፊዎች ምስጋና ካመሰገኑ በኃላ፤ ኮንፈረንሱ በምርምር፣ በፈጠራ እና በማሕበረሰብ ተሳትፎ መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል ።

በተጨማሪ የምርምር ውጤቶች ወደ ተግባራዊ መፍትሄዎች እና ከፖሊሲ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ጠልቃ ገብነቶች እንዲተረጎሙ ለማረጋገጥ ከመንግስት ተቋማት ፣ከኢንዱስትሪ እና ከልማት አጋሮች ጋር ሽርክናዎች ማበረታታችን እንቀጥላለን ብለዋል።

ልህቀት በጥረት!

ኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ

Written by 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *