በኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ የስነምግባርና ፀረሙስና ቀን ተከበረ።

ኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ፣ ሕዳር 26/2018 ዓ/ም በኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ በስነ ምግባርና መከታተያ ስራ ኣስፈፃሚ አዘጋጅነት “ትውልድን በስነምግባር ተቋምን በአሰራር በሚል ” መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ለ22ኛ ግዜ በሀገራችን ደግም ለ21ኛ ግዜ የዩኒቨርሲቲው ኣመራሮች፣ የዩኒቨርቲው ሰራተኞችና የማእከላዊ ዞን የስነምግባር ፀረሙሱና አመራሮች በተገኙበት የስነምግባርና ፀረሙስና ቀን ተከብረዋል ። በመክፈቻ ስነ ስርዓት የስነምግባር መከታተያ ስራ አስፈፃሚ ቀሲስ ኣረጋዊ ለገሰ የትምህርት ተቋማት ትውልድ የሚቀረፅበት ቦታ በመሆኑ ሁላችንን በተሰጠን ሓላፊነት ከሙስና የፀዳ ስራ መስራትና ብልሹ አሰራርን የሚፀየፍ ትውልድ በማፍራት ህዝባችን ማገልገል አለብን የሚል መልእክት አስተላልፏል ። ይህ በእንዲህ እያለ የዩኒቨርሲቲው ፕረዚዳንት ፕሮፌሰር ገ/የሱስ ብርሃነ በበኩላቸው ችግር ከተፈጠረ ሳይሆን ችግር ከመፍጠሩ በፊት ሕ/ሰብ መንቃት እንደአለበት ገልፀው፣ ዩኒቨርሲቲው የኛ ነው በሚል ሀሳብ “ ትውልድን በስነምግባር ተቋምን በአሰራር “ የሚለውን መሪ ቃል በተግባር ለማሳየት በቁርጠኝነትና መስራትና ብልሹ አሠራርን በመቃወም ብቁ ዜጋ መፍራት እንደሚጠበቅብን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡ በዚህ መድረክ፣ የስነምግባር ፅንሰ ሃሳብ፣ ኣስፈላጊነት እና ልናዳብራቸው የሚገቡ እሴቶች በመ/ር ሓጎስ ትኩእ ከኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ የስነምግባርና ስነ ዜጋ፣ እንዲሁም የስነምግባርና ሙስና ዝምድና በኣቶ ገ/መድህን ኣብርሃ ከማእከላዊ ዞን የስነምግባርና ፀረሙሱና ፅሕፈት ቤት የፀረ ሙስና እና መከላከያ ቡዱን መሪ በሚል የመወያያ ፅሑፍ ቀርበው ፣ በቀረቡት መወያያ ፅሑፍ መሰረት በማድረግ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቸነሱ ሲሆን በአዘጋጆቹ መልስ እና አስተያየት ተሰጥቶበታል ።

ልህቀት በጥረት!

ኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ

Written by