የመምህራንና ት/ት ቤት ኣመራሮች ልዩ የክረምት ኣቅም ግንባታ ለሰልጣኞች ማብራሪያ (orientation) ተሰጠ።

ሓምሌ 27/2017 ዓ/ም በኣኽሱም ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ የመምህራንና ት/ት ቤት ኣመራሮች ልዩ የክረምት ኣቅም ግንባታ ለሚከታተሉ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከትግራይ ትምህርት ቢሮ ተወካዮች በተገኙበት ማብራሪያ ተሰጥቷል ።

በዚህ የመክፈቻ ስነስርዓት የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ተወካይ እና የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕረዚዳንት ዶ/ር ኣብራሃም ነጋሽ ተገኝተው ሰልጣኞች እንደ አምና ጥሩ ውጤት ለማምጣት ጠንክራችሁ ማጥናት አለባችሁ ሲሉ ለሰልጣኞች መልእክት አስተላልፈዋል ።

ከዚህ በተጨማሪ ልዩ የክረምት የመምህራን እና ትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ ተጠሪ እና የአከዳሚክ ም/ፕ ተወካይ ዶ/ር ኣለምብርሃን ኣሰፋ የስልጠና ኣላማ፣ ምንነት እና ሰርቲፊኬት የ2016 የስልጠና ክንውን፣ የ2017 ዓ/ም ቅድመ ዝግጅት እና ትግበራ የሚመለከት ማንዋል(ፅሑፍ) ካቀረቡ በኃላ በዚህ እመት ለ1739 መምህራን ስልጠና እንደሚሰጥና ከነዚህ 226 የትምህርት ቤት ኣመራሮች መሆናቸውና ስልጠናው ከነገ 28/11/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 26 ቀናት እንደሚካየድ ገልፀዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ተወካይ ኣቶ ተክሌ ዘለቀ የስልጠናው ይዘት በአድሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት በሚያስተምሩበት ትምህርት የኣቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሰጥ እና በኢ/ያ በሠላሳ የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን ከነዚህ ኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ ኣንዱ ነው ብለዋል። ከዚህ በተያያዘ የትግራይ ትምህርት ቢሮ ተወካይ ኣቶ ኪዳነ ብርሃነ ሰልጣኞች ስልጠናው በአግባቡ መከታተል እንዳለባቸው ኣክለው ገልፀዋል ።

ስለ መኝታ ፣ምግብ ቤት፣ ቤተ መፅሓፍትና ድጅታል አጠቃቀም በሚመለከታቸው ኣካላት ኦረንቴሽን ተሰጥተዋል።

እንደ ሚታወቀው ስልጠናው ባለፈው ኣመት በተፈጥሮ ሳይንስ እና የትምህርት ቤት ኣመራር የተጀመረ ሲሆን ዘንድሮ ለየት የሚያደርገው የህብረተሰብ ሳይንስ ለመጀመሪያ ግዜ ስልጠና መስጠት መጀመሩ ነው።

ልህቀት በጥረት!

ኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ

Written by