ኣኽሱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹ በደማቅ ሁኔታ እየተቀበለ ይገኛል።

ኣኽሱም ዩኒቨርስቲ ዛሬ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት 1928 ወንድ ፣ 1132 ሴት ተማሪዎች በጠቅላላ 3060 ሪሚድያል ያለፉ እና መደበኛ ኣንደኛ ኣመት ተማሪዎች በደማቅ ሁኔታ እየተቀበለ ይገኛል። ውድ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ ጥንታዊትዋ ፣ ውቢትዋ እና የታሪክ እምብርት ወደ ሆነችው ኣኽሱም ከተማና ኣኽሱም ዩኒቨርስቲ በሰላም መጣችሁ እያልን ወደ ኣኽሱም ከተማ እንደደረሳችሁ በአየር መንገድ፣ መነሃርያና ፀሓይ በርቂ የዩኒቨርስቲው አውቶብሶች የሚጠብቋችሁ እና ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያደርሷችሁ ይሆናል። በከተማው በአየር መንገድ፣ መናሃርያና ፀሓይ በርቂ በተማሪዎች ህብረት የተመደቡ ኣስተባባሪዎች፣ የዩኒቨርስቲው ሰራተኞችና የከተማው ፀጥታ ኣካላት ባጅ ያላቸው በክብር የሚቀበሏቹ ይሆናል። በድጋሜ እንኳን በደህና መጣችሁ!! ኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ

Written by 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *