አስደሳች ዜና
አገራዊ የ2017 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፤
አክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ/ም የተሻለ የመውጫ ፈተና ውጤት ለመምጣት አቅዶ ከፍተኛ ርብርብ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በሰኔ 2017 ዓ/ም በተካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻችን በሁሉም የትምህርት መርኃ ግብሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ዘንድ መሀል 94.28% የማለፍያ ውጤት በማምጣት በከፍተኛ ሁኔታ ማለፍ በመቻላቸው ዩኒቨርሲቲው የተሰማው ደስታ ለመግለፅ ይወዳል።
ተማሪዎቻችን ጊዚያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ከማድረግ ባሻገር በተለያዩ ትምህርርት ክፍሎች የሚገኙ መመህራን የቱቶሪያል ድጋፍ እንዲሰጡ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል። በዚህም የተነሳ መምህራኖቻችን ያላቸውን እውቀትና ልምድ ሳይሰስቱ በመስጠት ለተማሪዎቻችን አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ከፍተኛ ድርሻ ተወጥቷል፡፡ የዩኒቨርቲያችን የአስተዳደር ሰራተኛም ለተማሪዎቻችን ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አኳያ ሌት ከቀን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር በሁሉም እርከን የሚገኝ የዩኒቨርሲቲያችን አመራር በቁርጠኝነትና በትብብር መንፈስ ሰፋፊ ስራዎች ሲሰራ ነበር፡፡
በመጨረሻም እነሆ በጥብቅ ዲሲፕሊን ያስፈተናቸው ተመሪዎቻችን እጅግ አስደሳች ውጤት ለማስመዝገብ ችሏል፡፡
እንኳን ደስ ያለን!
ልህቀት በጥረት!
ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ