አክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮለጅና ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ፤ ሚያዝያ 04 ቀን 2018 ዓ.ም
~የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮለጅና ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከተማሪዎች ጋር የምሳ ግብዣ ተካሄደ። በመቀጠልም በሆስፒታሉ በተኝተው ታካሚዎች በመዘዋወር የእንኳን ኣደረሳችሀ መልእክት ኣስተላልፈዋል። በመርኃ-ግብሩ ላይ የኮሌጁ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ገብረሂወት ተክለሃይማኖት ፣ የአካዳሚክና ምርምር ዋና ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር ተክለሃይማኖት ሕሉፍ ፣የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዲን ዶ/ር ሃፍቶም ከበደ፣ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች ዲን መ/ር ሰለሙን ሓጎስ ፣የጠቅላላ አገልግሎት ስ/አስፈፃሚ አቶ ፍስሃ መኮነን ና ሌሎች የሆስፒታልና የተማሪዎች አገልግሎት ኣመራሮች እና የኮሌጁ የተማሪዎች ህብረት አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል።
~በኮሌጁ የተማሪዎች ካፌ በተዘጋጀው በዚህ ልዩ የግብዣ ፕሮግራም ላይ የኮሌጁና ሆስፒታሉ አመራሮቹ ከተማሪዎችና ከታካሚዎች ጋር በመሆን በዓሉን ያከበሩ ሲሆን፣ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የኮሌጁና ሆስፒታሉ ማህበረሰብም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
መልካም የትንሳኤ በዓል!




