በአክሱም ዩኒቨርሲቲ 11ኛ ሃገራዊ የምርምር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል

አክሱም ዩኒቨርሲቲ፣ ታሕሳስ 16/2018 ዓ.ም

አክሱም ዩኒቨርሲቲ “በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ለማህበራዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል ከታሕሳስ 16 እስከ 17ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ 11ኛው ሃገራዊ የምርምር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።

በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት፣ እንዲሁም የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር አብርሃም ነጋሽ ተገኝተው ለተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ መልክት ካስተላለፉ በኃላ ፤ ዶ/ሩ በመልእክታቸው ዩኒቨርሲቲዎች የመማርና የማስተማር ብቻ ሳይሆኑ ሃሳቦች የሚፈተኑበት፣ እውነት የሚፈጠርበት እና ለእውነተኛ ማህበራዊ ችግሮች ተግባራዊ መፍትሄዎች የሚዳሰሱበት ቦታዎች ናቸው ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር መኮነን አረጋይም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ሲያስተላልፉ ዩኒቨርሲቲው ከኢንዱስትሪው እና ከማህበረሰቡ ጋር ጠንካራ አጋርነት በመፍጠር የአካዳሚክ ምርምርን ወደ ተጨባጭ መፍትሄዎች ለመምጣት ያለውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ልዩ ረዳት ዶ/ር ደስታ ገ/ተኽለ አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው የምርምር እይታ አቅርቧል ።

የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ሃላፊ ዶ/ር አፅብሃ ገ/ሄር የመወያያ ፅሁፍ አቅርበዋል። በቀረበው ፅሁፍ ላይ ተሳታፊዎች አስተያየትና ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ዶ/ር አፅብሃ ገ/ሄርም መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

11ኛው ሃገራዊ የምርምር ኮንፈረንስ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል። በኮንፈረንሱ ላይ የአክሱም፣ የመቐለ፣ የዓዲ ግራት እና የራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተመራማሪዎች የምርምር ፅሁፋቸውን ያቀርባሉ።

ልህቀት በጥረት!

ኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ

Written by 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *