ክሱም ዩኒቨርስቲ ለአቅም ማሻሻያ (remedial) ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃግብር እና የማብራርያ (Orientation) መድረክ አካሄደ ።

ኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ : ታህሳስ 08/2018 ዓ/ም

አክሱም ዩኒቨርስቲ ዛሬ 08/04/2018 ዓ/ም በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ አዲስ ገቢ አቅም ማሻሻያ(remedial) ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ማብራርያ (orientation) አካሂደዋል ።

በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫና የማብራሪያ (Orientation ) መርሃግብር የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአካዳሚክ ዳይሬክተር ተወካይ ዶ/ር ገብረመድህን ገብረሃወርያ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ከስተላለፉ በኃላ የመጣቹበት ዓላማ ትምህርትና ትምህርት ብቻ ስለሆነ ጠንክራችሁ በማጥናት ውጤታማ መሆን ይገባችኋል በማለት መልአክታቸው ስያስተላልፉ ፤ አክለው ለናንተ ለማገልገልና ለማገዝ ዝግጅ ነን ብለዋል።

በተጨማሪ የተማሪዎች ምክትል ዲን የሆኑት መምህር ዘለአለም ሐጎስ ስለተማሪዎች መብትና ግዴታ በተመለከተ ተማሪዎች ማድረግ ያለባቸውና የሌለባቸው እንዲሁም ማግኘት ያለባቸው ጥቅሞች ሰፋ ያለ ማብራርያ ሰጥተዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ በዚህ መድረክ የተገኙ የአካዳሚክ ም/ፕ ዶ/ር ሙሉጌታ በሪሁ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ካቀረቡ በኃላ የዩኒቨርሲቲው አመራርና ማሕበረሰብ ለናንተ ድጋፍ ለመስጠት ቁርጠኛ ነው ብለዋል። ዶ/ር ሙሉጌታ አያይዘው ተማሪዎች በርትተው በማጥናት በሃገር የሚሰጥ ፈተና ጥሩ ውጤት አምጥተው እንዲያልፉ ምኞታቸው ገልፀዋል።

በመጨረሻ የሬጂስትራር ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ የሆኑት መምህር ዜናዊ ክፍላይ በፕሮግራሙ ተገኝተው ስለ ተማሪዎች ምዝገባ ፣ ውጤትና የተማሪዎች ቆይታ የመሳሰሉትን ህግና ደምብ አብራርተዋል።

ልህቀት በጥረት!

ኣኽሱም ዩኒቨርሲቲ

Written by