AksumUniversity
በአኽሱም ዩኒቨርሲቲ በወረቀት እና በበየነ መረብ (On line) ሲሰጥ የቆየ የአገር አቀፍ 2ኛ ደረጃ የመልቀቅያ ፈተና በሰላም እና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ።
በአኽሱም ዩኒቨርሲቲ በበይነ መረብ ሲሰጥ የቆየው የማኅበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም በሰላም ተጠናቋል።
ጠቅላላ ተማሪዎች: ከ13,900 በላይ
የትምህርት ዘርፎች: ተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ
የመጡበት ዞኖች: ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ማእከላይ ዞን
ዓይነት: የአገር አቀፍ የ2ኛ ደረጃ የመልቀቂያ ፈተና
የምዘና ሂደቱ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጾ ምስጋና ይገባቸዋል ተብለዋል፤ በዋናነት:
ላደረጉት ድጋፍና ትብብር ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል።
በፈተናው አሰጣጥ ሂደት ተፈታኞች የፈተና ደንብን ባከበረ መልኩ ፈተናቸውን ሲወስዱ መታየታቸውም በፈተና ሂደቱ ለተስተዋለው ፍፁም ሰላማዊነት የላቀ አስተዋፆ እንዳለው የፈተና አስተባባሪ ኮሚቴዎች ገልፀዋል፤ ተፈታኞች ለደንብና ስርዓት በመገዛት ፈተናው ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላሳዩት ታዛዥነት ሊመሰገኑ ይገባል በማለት መልካም ውጤት እንዲገጥማቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ልህቀት በጥረት!