የከተማዉ ህዝብ ከዩኒቨርሲቲዉ ጎን መቆሙን ገለፀ

Fresh11.jpg

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለ2010 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ለተቀበላቸዉ  የመጀመሪያ  አመት ተማሪዎች የገለፃ (የኦሬንቴሽን) ኘሮግራም ተዘጋጀ ፡፡ በዝግጅቱ ላይ የዪኒቨርሲቲዉ የአመራር አካላት የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ተወካዮች የሃይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች የተገኙ ሲሆን የዩኒቨርሲቲዉ ኘሬዚዳንት ዶ/ር ፀሃየ አስመላሽ ባሰሙት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የኢትዮጵያ የ3000 ዘመን ታሪክ ማእከል ወደ ሆነችዉ አክሱም ዩኒቨርሲቲ መመደብ የቀደመዉን ታሪካችን ለመመርመር እና የወደፊቱን ለማመልከት ትልቅ አጋጣሚ የሚፈጥር መልካም እድል ነዉ በማለት እንግዳ አክባሪ ህዝብ መሃል በመሆናችሁ ከተማዉ ዉስጥ በነፃነት መንቀሳቀስ እንደምትችሉ ለረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል ፡፡ የአገር ሽማግሌዎቹንና የከተማዉ ህ/ሰብ ወክለዉ የተናገሩት መምህር ይትባረክ ገ/ህይወት በበኩላቸዉ አገሪቱ እና ወላጆቻችሁ የስጥዋችሁ አደራ እንድትወጡ በመማር ማስተማር ሂደት የሚገጥማቹሁ ችግሮች ለመፍታት ከጎናችሁ ነን ብለዋል ፡፡