የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምርቃ በአል ተከናወነ

G7_0_0.jpg

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸዉ 2500 ተማሪዎች ሰኔ 24/2009 ዓ/ም አስመረቀ ፡፡ ዘንድሮ በተከናወነዉ ዘጠነኛ ዙር የተማሪዎች ምረቃ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብሮች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያስለጠናቸዉ 1011 ሴት እና 1489 ወንድ በድምሩ 2500 ተማሪዎች ለምረቃ የቀረቡ ሲሆን  ከነዚህ ዉስጥ 11 ሴቶች እና 77 ወንዶች በድምሩ 88 ተማሪቂዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸዉ ፡፡ ከተመራቂዎቹ ዉስጥ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሰለጠኑ የመጀመሪያ ዙር 26 የህክምና ዶክተሮች ይገኙበታል ፡፡

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ኘሬዚዳንት ዶ/ር ፀሃዬ አስመላሽ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልእክት በትምህርት ቆይታቹሁ የቀሰማችሁትን የፅንስ ሃሳብ እዉቀት ወደ ተግባር በመቀየር የሃገሪቱን የልማት አቅጣጫ የመደገፍ ኋላፊነታችሁን የምትወጡበት ወቅት አሁን ነዉ ብለዋል ፡፡

የላቀ የትምህርት ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪወች ሜዲልያና የምስክር ወረቀት የሰጡት የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ርመ ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ በበኩላቸዉ ተማራቂዎች በቆይታቸዉ የቀሰሙት ዕዉቀትና ክህሎት አገራችን  ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ  ለመገንባት በምታደርገዉ ፈጣን ሂደት ኢንዱስትሪዉ ተወዳዳሪ እንዲሆን ኢኮኖሚዉ ደግሞ መዋቅራዊ ለዉጥ እንዲያስመዘግብ እንዲጠቀሙበት  አሳስበዋል ፡፡