የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ግምጋማዊ ውይይት ተጀመረ

MM3_0.jpg

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ከዛሬ መስከረም 08-12/2010 ዓ/ም ድረስ የሚቀጥል ግምገማዊ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት ማህበረሰብ ግምጋማዊ ስልጠና ባዘጋጀው መርሃ ግብር መሰረት ስልጠናው የሚከተሉት አምስት ርእሶች አሉት

  1. መምህርነት ቅድመሁኔታ የማይገድበው ባለአደራነት
  2. የውጤታማ ትግበራ ስኬት አሰራር ስርዓት በከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችን ምን፣ ለምንና እንዴት
  3. የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት ስኬቶች ክፍተቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች
  4. በጥልቅ ተሃድስዎቻችን የተለዩ ችግሮች የተቀየረው ሁኔታና ቀሪ ስራዎች
  5. የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የ2009 ዓ/ም እቅድ አፈፃፀምና የ2010 ዓ/ም እቅድ

በዚሁ መሰረት የዩኒቨርሲቲው ምምህራንና ሰራተኖች በአክሱም ዋናው ካምፖስና በሽሬ ካምፖስ በተዘጋጁ የመወያያ ፅሁፎች ላይ ትኩረት አድርገው በቡዱንና በጋራ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡