የአንደኛ አመት ተማሪዎች ቅበላ

WelF2.jpg

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የ2010 ዓ/ም የመጀመሪያ ዓመት (Fresh) ተማሪዎች ቅበላ ተጀመረ::   በተያዘው የቅበላ  መርሃ ግብር መሰረት አዲስ ተማሪዎች ከ28-29/01/2010 ዓ/ም ድረስ በዩኒቨርሲቲው ተገኝተው ሪፖርት ማድረግ ያለባቸው ሲሆን በዚሁ መሰረት ቁጥራቸው በርከት ያሉ ተማሪዎች ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በመግባት ላይ ናቸው:: ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ የራሱን መኪኖች በአክሱም አፄ ዮሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያና በከተማው የመንገደኞች መናሃርያ በማሰማራት ተማሪዎቹን በመቀበል ላይ ነው::