የቱሪዝም ዓዉደ ጥናት ተከፈተ

Hidar1.jpg

 

 

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር “ ህዳር ጽዮን ፌስቲቫል ለቱሪዝምና ዘላቂ ልማት ” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀዉ አዉደጥናት ዛሬ ህዳር 19/03/2010 ዓ/ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ አዲሱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ ፡፡

በመድረኩ የህዳር ጽዮን በአል ለቱሪዝም እድገት እያደረገ ያለዉ አስተዋፅኦ ፣ ማህበረሰብ አቀፍ የቱሪዝም ልማትና ተጠቃሚነት እንዲሁም የባለ ድርሻ አካላት ሚና በህዳር ፅዮን በአል አከባበር በሚሉ ርእሶች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጡ በዶ/ር ተክለሃይማኖት ገ/ስላሴ ፣ ዶ/ር ሙሉጌታ ፍስሃ እና አቶ ተክሌ ሓጎስ በቅደም ተከተል ጥናቶች ቀርበዋል ፡፡

 

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ኘሬዚዳንት ዶ/ር ፀሃዩ አስመላሽ አዉደ ጥናቱን ሲከፍቱ መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ የተለየ ትኩረት በመስጠት ስትራቴጂ ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን እና አክሱም ዮኒቨርሲቲም ይህን የመንግስት አቅጣጫ አንድ የስራ አካልና የልህቀት ማዕከል ለማድረግ ለስራዉ ስኬት የአርኪዮሎጂና ቱሪዝም ኢንስቲትዮት ከፍቶ በስራ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል ፡፡

የአክሱም ከተማ የቱሪዝም የስራ ሂደት ሃላፊ አቶ ገ/መድህን ፍ/ብርሃን በበኩላቸዉ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ያልለሙ የቱሪዝም መስህቦች ለምተዉ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆኑ እያደረገ ያለዉ እንቅስቃሴ ሊበረታታ ይገባል ብለዋል፡፡