አክሱም ዩኒቨርሲቲ “ የቅዱስ ያሬድ ስራዎች ለዘላቂ የቱሪዝም ልማት “ በሚል መሪ ሓሳብ ዐዉደ ጥናት አካሄደ

Y2_0.jpg”ቅዱስ ያሬድን ሳናውቀው እንዴት እናስተዋውቀዋለን?” መ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማሪያም“በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዓለም ላይ የነገሱት ዘመናዊ የሙዚቃ መሳርያዎች ከቅዱስ ያሬድ የዜማ መሳርያዎች የተወሰዱ ናቸዉ ፡፡” ዶ/ር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄየ ቅዱስ ያሬድ ስራዎች በአግባቡ ተጠንተዉ ለቱሪዚም ልማት ማዋል ይገባል' የዐዉደ ጥናቱ ተሳታፊዎችአክሱም ዩኒቨርሲቲ “ የቅዱስ ያሬድ ስራዎች ለዘላቂ የቱሪዝም ልማት “ በሚል መሪ ሓሳብ ዐዉደ ጥናት አካሄደመድረኩን የከፈቱት የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ኘሬዚዳንት ዶ/ር ፀሃዬ አስመላሽ ዩኒቨርሲቲዉ የቅዱስ ያሬድ ስራዎች ለዓለም ለማስተዋወቅ በስራዎቹ ዙርያ ተጨማሪ ጥናቶች እንደሚካሄድ ያበረታታል ብለዋል ፡፡በዐዉደ ጥናቱ የቅዱስ ያሬድ አስተዋፅኦ የሚዳስሱ 12 ጥናቶች ቀርበዋል ፡፡በጥናቶቹ የቅዱስ ያሬድ ትዉልድና እድገት ፣ ለዘመናዊ ስነ ፅሁፍ ፣ ሙዚቃ፣ የዘመን ቀመርና ሌሎች አስተዋጽኦዎቹ ተዳስሰዋል ፡፡የቅዱስ ያሬድ ትዉልድና እድገት በተመለከተ ጥናት ያቀረቡት ረዳት ኘሮፌሰር አየለ መኩሪ  ቅዱስ ያሬድ በአክሱም የአብነት ትምህርት እየተከታተሉ ማደጉን አንስተዋል ፡፡ዶ/ር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ዓለም ላይ የነገሱት ዘመናዊ የሙዚቃ መሳርያዎች ከቅዱስ ያሬድ የዜማ መሳርያዎች የተወሰዱ ናቸዉ ፡፡  ሲል አስቀምጠዋል ፡፡ የቅዱስ ያሬድ ፍልስፍና ጽብራቆ ያቀረቡት መም/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም “ ይቻላል “ የጀመረዉ ቅዱስ ያሬድ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡ ስራዎቹ ለማስተዋወቅ መመራመር እንደሚያስፈልግ ለማጠየቅ “ ቅዱስ ያሬድን ሳናዉቀዉ እንዴት እናስተዋዉቃለን ? በማለት  ለታሪካችን ቀዳሚነት ሰጥተን መሰነድ እንደሚገባን አስረድተዋል ፡፡ዶ/ር ሙሉጌታ ፍስሃ በበኩላቸዉ ቅዱስ ያሬድ ልዩ ልዩ ስራዎችን ያከናወነባቸዉ ቦታዎች በኢኮ ትሪዝም ማልማት እንደሚገባ መክረዋል ፡፡ የአዉደ ጥናቱ ተሳታፊዎች የቅዱስ ያሬድ ስራዎች በአግባቡ ተጠንተዉ ለቱሪዝም ልማት ማዋል ይገባል ብለዋል ፡፡አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በመተባበር በተዘጋጀው ዐውደ ጥናት ታላላ አርቲስቶች የሃይማኖት መሪዎች ምሁራንና የአክሱም ነዋሪዎች ተሳተፈዋል' በዕለቱ በዶ/ር ሙሉጌታ ፍሰሃ የተፃፈ በኢትዮጵያ የቱሪዝም ልማት ያጠነጠነ መፅሓፍ ተመርቀዋል'