በሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ኘሮግራም አበረታች ዉጤት ተመዘገበ

shared campus 10.jpg

shared campus 1.jpg

shared campus 7.jpg

shared campus 4.jpg

ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ በ2010 ዓ/ም በትግራይ ክልል በሚገኙ ሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም በአክሱም ፣ መቐለ እና ዓድግራት ዩኒቨርሲቲዎች የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ባቀረበዉ ጥያቄ መሰረት በ8ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ዉጤት ያመጡ ተማሪዎች እያንዳንዳቸዉ 30 ተማሪዎች በመቀበል የሳይንስ ( ስነ ህይወት ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና አይቲ ) ትምህርታቸዉን በአቅራቢያ ዩኒቨርሲቲ እንዲከታተሉ የተጀመረ ኘሮግራም ነዉ ፡፡

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በከተማዉ ካሉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተዉጣጡ በ8ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ዉጤት ካመጡ ተማሪዎች በሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች የተዘጋጀ የመግቢያ ፈተና ከወሰዱ 57 ተፈታኞች 30 ተማሪዎች በሳይንስ ዘርፍየማጠነናከርያ ትምህርት በመሰጠት ላይ ይገኛል ፡፡

ኘሮግራሙ የዩኒቨርሲቲዉየማህበረሰብ አገልግሎት አካልሲሆን የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ለመገምገም ባሳለፍነዉ ቅዳሜ የካቲት 3/2010 ዓ/ም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በተዘጋጀ መድረክ እንደተገለፀዉ አበረታች ዉጤት እየተመዘገበበት ነዉ ፡፡

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ኘሬዚዳንት ዶ/ር ምስግና ገ/ህይወት እንደገለፁት አክሱም ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ትምህርቶች ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት እየሰራ ሲሆን የዚሁ ማሳያ የሆነዉ ግንባታዉ በመካሄድ ላይ ያለዉ የዩኒቨርሲቲዉ የሳይንስ ሙዜም በአብነት ጠቅሰዉ ! የሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ኘሮግራም አንዳንድ ችግሮች እየታዩበት ያለዉ የአገራችን የትምህርት ጥራት ለመደገፍ የበኩሉን ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት ነዉ ብለዋል ፡፡